A historic place of worship
ከ180 ዓመታት በላይ ታሪክ ያለው መንፈሳዊና ታሪካዊ ቅርስ
Our church was established in 2008 and registered as a charity in England and Wales in 2009. In 2017, the congregation acquired the former St John the Evangelist Church in Higher Broughton, Salford, as its permanent place of worship. Designed by Richard Lane and built between 1836 and 1839, the building is Grade II listed. Its grounds also contain a historic First World War memorial cross.
ደብራችን በ2000 ዓ.ም. (2008 እ.ኤ.አ.) የተመሠረተ ሲሆን፣ በ2001 ዓ.ም. (2009 እ.ኤ.አ.) በጎ አድራጎት ድርጅትነት ተመዝግቧል። በ2009 ዓ.ም. (2017 እ.ኤ.አ.) ታሪካዊውን St John the Evangelist Church ገዝቶ ቋሚ የአምልኮ ስፍራ አድርጎታል። ሕንፃው ከ1836 እስከ 1839 እ.ኤ.አ. በRichard Lane የተገነባ Grade II ቅርስ ነው። በግቢውም የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት መታሰቢያ መስቀል ይገኛል።
View Historic England Grade II listing
A spiritual home for our community
ለሺህዎች መንፈሳዊ ተስፋ የሚሆን ማዕከል
Our parish serves more than 1,000 worshippers and community members. It is a spiritual and cultural meeting place for Ethiopian and Eritrean Orthodox Christians and others across Greater Manchester. Manchester’s transport connections also make it a potential gathering place for visitors from across the UK for major religious celebrations.
ደብራችን ከ1,000 በላይ ምእመናንን የሚያገለግል ሲሆን፣ ለኢትዮጵያውያን፣ ለኤርትራውያንና ለሌሎች የኦርቶዶክስ ክርስትና ተከታዮች መንፈሳዊና ማኅበራዊ ትስስር የሚፈጥር ማዕከል ነው። ማንቸስተር ካላት ምቹ የመጓጓዣ ትስስር አንፃር፣ ከተለያዩ የዩኬ አካባቢዎች ለሚመጡ ምእመናንም አገልግሎት የመስጠት አቅም አለው።
More than a church building
ሰፊ ግቢና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል አቅም
The site includes a spacious churchyard and, according to church records, 32 rooms beneath the main building. The congregation also identifies a natural underground spring within the grounds, traditionally associated with Holy Water (Tsebel). Following restoration, safety assessment and the necessary permissions, we hope the site will support Divine Liturgy, traditional Abnet and Sunday School education, children’s programmes, Holy Water and spiritual retreats, pastoral care and heritage learning.
ደብራችን ሰፊ ግቢ አለው። በደብሩ መረጃ መሠረት ከሕንፃው በታች 32 ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ በግቢው ውስጥም ከመሬት በታች የሚፈልቅ የተፈጥሮ የጸበል ምንጭ እንዳለ ደብሩ ያስታውቃል። ከተገቢው እድሳትና የደኅንነት ማረጋገጫ በኋላ ለቅዳሴ፣ ለአብነትና ለሰንበት ትምህርት፣ ለሕፃናትና ለወጣቶች፣ ለጸበል፣ ለሱባዔ፣ ለማኅበራዊ እንክብካቤና ለታሪክ ጥበቃ እንዲውል እንመኛለን።

Why restoration is urgently needed
የአሁኑ ሁኔታ – እድሳት የሚፈልግ ታሪካዊ ሕንፃ
The historic building is currently closed for worship because of its condition and significant repair needs. Our congregation continues services at a temporary place of worship. Working with professional assessments and heritage conservation guidance, the church is planning repairs to protect the structure, improve safety, address drainage and electrical needs, conserve the windows and preserve the building’s character.
ታሪካዊው ሕንፃ በደረሱበት ጉዳቶችና በከፍተኛ የጥገና ፍላጎት ምክንያት ለአምልኮ አገልግሎት ዝግ ሆኗል። ምእመናን በጊዜያዊ የአምልኮ ስፍራ እያመለኩ ይገኛሉ። ደብሩ የሕንፃውን ደኅንነት ለማረጋገጥ፣ የተጎዱ ክፍሎችን ለመጠገን፣ የውኃ ፍሳሽንና የኤሌክትሪክ ሥርዓቶችን ለማሻሻል እና ታሪካዊ ገጽታውን ለመጠበቅ እየሠራ ነው።
Our vision for the future
የነገ ራእያችን
This project is about more than restoring an old building. We want to preserve a living heritage and create a lasting spiritual, educational, cultural and community centre for future generations. We welcome the support of worshippers, businesses, heritage organisations, charitable foundations and our wider community.
ዓላማችን ታሪካዊ ሕንፃን መጠገን ብቻ አይደለም። ለአሁኑና ለመጪው ትውልድ ዘላቂ መንፈሳዊ፣ ትምህርታዊ፣ ባህላዊና ማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል መፍጠር ነው። የምእመናን፣ የደጋፊዎች፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና የቅርስ ጥበቃ ተቋማት ትብብር እንፈልጋለን።


















